አጭር ያሠራር መመሪያ

ግዳጅ

ይኸን ፕሮግራም ያለምንም ችግር ለማስነሳትና ለመጠቀም ቢያንስ JRE 1.4 (Java Running Enbironment) ወይም J2SE 1.4 (Java Software Development Kit) ሲሰተሙ ላይ በቅድሚያ መተከል አለበት።

አነሳስ

ቀጥለው በሚታዩት ሦስት መንገዶች ሳድስን ለሥራ ማስነሳት ይቻላል።

  1. ሳድስን ካማርኛ ያሠራር መመሪያ ጋር ማስነሳት

    javaw -classpath . Sadiss am ET
  2. ሳድስን ከእንግሊዘኛ ያሠራር መመሪያ ጋር ማስነሳት

    javaw -classpath . Sadiss
  3. ሳድስን ካሜሪካ እንግሊዘኛ ያሠራር መመሪያ ጋር ማስነሳት

    javaw -classpath . Sadiss en US

ኪቦርድ አሠራር

የኢትዮጵያ ፊደላትን ለመጻፍ ፥ የሳድስን ኪወክ ኪቦርድ ሥርዓት መጠቀሙ በቂ ነው። የቀረቱን የዩንኮድ ሆሄያትን ለመጻፍ ግን የኪወክ ኪቦርድ ሥርዓት ችሎታ የለውም። ይሁን እንጂ ፊደላቱን በኮዳቸው አማካኝነት መከተብ እንችላለን። አጠር ያለ ዝርዝር እነሆ፦

  1. ዩንኮድን ሆሄያት በተሰየሙት የኮድ ቁጥር በኩል መጻፍ ይቻላል። በዚህ መንገድ ሆሄያቱን ለመጻፍ ከሳድስ ቱልባር ላይ የይንኮድን ጠቅባይ (button) መጫን ይኖርብናል። ወይም ከክተባ ሜኒዩ ዩንኮድን መምረጥ ይኖርብናል። አስከትሎ በሚከፈተው መስኮት ውስጥ ፊደላቱን እንጽፋለን። ለምሳሌ ሀሁሂሃሄህሆ ለመጻፍ

    \u1200\u1201\u1202\u1203\u1204\u1205\u1206

    እናስገባለን።
  2. የኪወክ ኪቦርድ ሥርዓት ከዋሸራ የተወረሰ ነው። ኪወክ አጽህሮተ-ቃል ሲሆን የሚወክለው ያለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌን ስም ነው። ይህ የኪወክ ኪቦርድ ሥርዓት መደበኛ የኪቦርድ ቁልፎችን/ኪዎችን ከኢትዮጵያ ፊደላት ጋር ያዛምዳል። በዩንኮድ እስታንዳርድ የተቀመጡት የኢትዮጵያን ፊደላት በሙሉ መከተብ ይቻላል። ለኪወክ ኪቦርድ ሥርዓት ሠንጠረዥና ለዝርዝር ማብራሪያ ይኸን ለጣቂ ይመልከቱ።

ንባብ ክተባ

ሳድስ ሁለት ንባብ የመጻፊያ ዘይቤዎች አሉት።

  1. Ctrl+e ኪወክ ኪቦርድ ሥርዓት፦ በኢትዮጵያ ፊደል መጻፊያ ዘይቤ ነው። ሳድስ ሲነሳ በተፈጥሮው የሚከተለው የኪቦርድ ሥርዓት ይኸ ነው። ወደ መደበኛው ወይም ላቲን ኪቦርድ ሥርዓት ለመቀየር Ctrl+e ይጫኑ።
  2. Ctrl+e መደበኛ ኪቦርድ ሥርዓት፦ በእንግሊዘኛ ፊደል መጻፊያ ዘይቤ ነው። ከኪወክ ኪቦርድ ሥርዓት ወደዚህ ለመቀየር Ctrl+e ይጫኑ።

ፋይል አፈጣጠር፥ አከፋፈት፥ አዘጋግ

ሳድስ ሲከፈት ስሙ ያልተሰየመ አዲስ ሰነድ ይፈጥርና ራሱን ለጽሁፍ ያዘጋጃል። እዚህ ደረጃ ላይ ሰነዱ ባዶ ስለሆነ ዲስክ ውስጥ ሳይሆን የሚፈጠረው በሳዲስ ሒልና ውስጥ ነው። ሳድስ ለያንዳንዱ ሰነድ ወይም ፋይል የግል መስኮት ይሰጣል። ይህ መስኮት መስኮተ-ሰነድ ይባላል።

የተፈጠረው ሰነድ ባዶ እንደሆነ መስኮተ-ሰነዱ ከተዘጋ፥ ሳድስ በሒሊናው ውስጥ ስለዛ ሰነድ ያቀፈውን ነገር በሙሉ በመጣል፥ የተከፈተውን መስኮተ-ሰነድ ይዘጋል።

የሳድስን የፋይል ሜኒዩ በመጠቀም አዲስ ሰነድ መፍጠር ወይም የቆየ ሰነድ መክፈት ይቻላል። ለዛ የፋይልን ሜኒዩ ወይም የቱልባሩን ጠቅባይ ይጠቀሙ።

ንባብን ወደ ፋይል መጻፍ

ሳድስ ሦስት የንባብ አይነቶች ይደግፋል። የንባብ አይነት መረጣው ከፍተኛ ጥንቃቄ ይጠይቃል። አንዱን ከሌላው ለይቶ መገንዘብ ግዴታ ነው። ሦስቱ የንባብ አይነቶች ከዚህ በታች ቀርበዋል።

  1. አስኪ (ASCII) የንባብ ቅርጽ፦ በእንግሊዘኛ የሚጻፉ ነገሮች በሙሉ እንደ አስኪ ይታያሉ። ወደ ዲስክ ለመክተት ማለትም ፋይል ውስጥ ለማስቀመጥ የፋይል ስሞች በ".txt" መቋጠር አለባቸው።
  2. ዩ.ቲ.ኤፍ የንባብ ቅርጽ፥ በኢትዮጵያ ፊደል የሚጻፉ ነገሮች በተለይ የዌብ ገጾች እንዲሁም የኤለክትሮኒክ መልክቶች በዩ.ቲ.ኤፍ መልክ ወደ ፋይል መጻፍ አለባቸው። የፋይል ስሞች በ".utf" መቋጠር አለባቸው።
  3. ዩንኮድ የንባብ ቅርጽ፦ ይህ የንባብ አይነት የዩንኮድ ንባቦችን ወደ ፋይል ለመጻፍ ወይም ከፋይል ለማንበብ ይረዳል። ይሁን እንጂ ፥ የሚፈጥራቸው ፋይሎች ከሳድስና ከተመሳሳይ ፕሮግርሞች ውጭ ትርጉም ላይኖረው ይችላል። ለምሳሌ ተጠቃሚው ፋይሉን የሚጠቀመው ከሳድስ ጋር ብቻ ከሆነ፥ የዩንኮድ የንባብ አይነት መገልገሉ ክፋት የለውም። ይህ ምርጫ መወሰድ ያለበት ንባቡን በዩ.ቲ.ኤፍ መልክ ፋይል ውስጥ መጻፍ ካልተፈለገ ብቻ ነው። የፋይል ስሞች በ".uni" መቋጠር አለባቸው።

ፎንት መረጣና ፎንት ቁመት አወሳሰን

ሳድስ አብሮት የሚመጣ ኢትዮጵያ ጅረት ተብሎ የሚጠራ የላቲንና የኢትዮጵያ ፊደል ዩንኮድ ፎንት አለው። ይሁን እንጂ ሌሎች ፎንቶች ካሉ፥ ተጠቃሚው እነዛን ፎንቶች የመጠቀም ምርጫ አለው።

ሳድስ ባንድ ሰንድ ውስጥ የሚፈቅደው የፎንት አይነት አንድ ብቻ ነው። ሰነዶችን እየጻፉ ከየትኛውም ነጥብ ሆኖ ፎንቶችን መቀየር ይቻላል። እንደዚሁ የፎንቶችን መጠን ማሳደግ ወይም መቀነስ ይቻላል።

ቃላት ወይም ሐረግ አፈላለግ

ባንድ ሰነድ ውስጥ የሆነ ቃል ወይም ሐረግ መኖርና አለመኖሩን፥ ካለ የተቀመጠበትን ቦታ አስሶ ማግኘት በጣም ቀላል ነው። ባንድ ተናጠል ሂደት ሰነዱ ውስጥ ቃሉ ወይም ሐረጉ የሚገኘበትን ቦታዎች በተከታታይ ማፈላለግ ይቻላል። ለተግባር ከከታቢ ሜኒዩ ቃል አሳሽን ይጠቀሙ።








Copyright © 2002 Senamirmir Project