የላተክ (LaTeX) ሰነድ አጻጻፍና አወጣጥ2.1 ምዕላደ-ቃላት
2.2 የሥራው ቅደም-ተከተልበዚህ ክፍል እንዴት አድርገን የLaTeX ሰነዶችን እንደምናዘጋጅ በተርታ እንመለከታለን። ሥራው የሚከተሉት ደረጃዎች ይይዛል።
ሂደቱን ጀምሮ ለመጨረስ በምዕራፍ ፩ የተዘረዘሩት ሶፍትዌሮች በሙሉ መኖርና መሥራት አለባቸው። ሌሎች አማራጭ ሶፍትዌሮች ካሉ የተጠቃሚው ፈንታ ነው። 2.3 በሳድስ ሰነድ አጻጻፍየLaTeX ጽሑፋችንን የምናዘጋጀው በኢትዮጵያ ፊደል መጻፊያ ፕሮግራም ሳድስ ነው። እንደ ምሳሌ የቀረቡት ሰነዶች በሙሉ የተጻፉት ሳድስን በመጠቀም ነው። ይህ ፕሮግራም፥ በዩንኮድ መልክ የተጻፉ ንባቦችን በትክክለኛ መንገድ ወደ ዲስክ የመጻፍና የማንበብ ችሎታ አለው። የTeX ወይም የLaTeX ፋይሎችን በውል ይረዳል። ሥራውን እንጀምር።
2.4 ጹሑፍን በላተክ ማዘጋጀትየሚቀጥለው ተግባራችን ጹሑፋችንን በላተክ ማዘጋጀት ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ ላተክ ጽሑፋችንን አንብቦ በተሰጠው መመሪያ መሠረት የመጨረሻውን ፋይል ያወጣል። ያንን ፋይል ማንበብ ወይም ማተም እንችላለን። ጽሑፋችንን በላተክ የምናዘጋጅበት መንገድ ከአንድ በላይ ነው። በዚህ ጥናት ውስጥ ግን pdflatexን እንጠቀማለን። በመሆኑም ተጠቃሚው የማንበቡን ሆነ የማተሙን ሥራ በቀላሉ ማካሄድ ይችላል። ግዴታው የአዶቢን ሪደር (Adobe Reader) መኖሩ አለበት ነው። የሚከተለው ቅደም-ተከተል መፈጸም ያለበት በዊንድስ ሥር ነው፤ ይሁን እንጂ ተፈላጊውን ለውጥ በማድረግ በልዪንክስ ሥር ተግባሩን መፈጸም ይቻላል።
2.5 ማንበብ ወይም ማተምበዚህ ሂደት ውስጥ በፒ/ዲ/ኤፍ መልክ የወጣውን ጽሑፋችንን ለማንበብ ወይም ለማተም መሞከር ነው። ሥራው እጅግ በጣም ቀላል ነው። ፒ/ዲ/ኤፍ አንባቢ ፕሮግራማችንን አስነስተን test.pdfን በመክፈት ጽሑፋችን ምን እንደሚመስል መመልከትና እንዳሥፈላጊነቱ ማተም እንችላለለን። አንድ በፍጹም መጠንቀቅ ያለብን ነገር አለ። ጽሑፋችንን እንደጠበቅነው ከወጣ መልካም፤ ነገር ግን በከፍተኛ ደረጃ ስናሳድገው (zoom in) ፊደላቱ ዳርዳራቸው ትንሽም ቢሆን መሸራረፍ የለበትም። ከሆነ ወደ ምዕራፍ ፩ ተመልሰን ከMikTeX Options ጋር የተያየዘውን የዝግጅት ሥራ መድገም አለብን። 2.6 ስህተቶችና አስተራረምየLaTeX ጽሑፍ ዝግጅት ለስህተቶች መፈጠር አመቺና ችግር ፈጣሪ ነው። ስህተቶች ሲከሰቱ የግድ መታረም አለባቸው ምንም እንኳን አንዳንዶቹ ለሥራው መካሄድ ሙሉ በሙሉ እንቅፋት ባይሆኑም። የስህተቶችን መኖርና አለመኖር በወል የምናውቀው ጽሑፋችንን በLaTeX በምናዘጋጅበት ወቅት ነው። LaTeX ስህተቶች ሲያጋጥሙት፥ የስህተቱን ዓይነትና ምንጩ የት እንደሆነ ይገልጻል። አብዛኛውን ጊዜ፥ ከስህተቶቹ መልክት መንስኤቸውን በቀላሉ መረዳት ይቻላል። አንዳንድ ጊዜ ግን፥ ምክንያቱን በግልጽ ማወቅ በጭራሽ ይቸግራል። ለማንኛውም ራስን ከስህተት ዓይነቶች ጋር ማዛመድ፥ መፍትሄዎችን በቀላሉ ለመሻት ይረድል። ይህ ማለት ምን ማለት ነው? አንድን ጽሑፍ በLaTeX ስናዘጋጅ፥ በውጤቱ እስከምንረካ ድረስ ሂደቱን መደጋገም የግድ ነው። በአጠቃላይ ደረጃ TeXን ከባድ ከሚያረጉት ምክንያቶች አንዱ ይህ ነው። |
||||||||||||||||||
Copyright © 2002-2005 Senamirmir Project