Senamirmir Senamirmir Projects Senamirmir Interviews Senamirmir Downloads Senamirmir Links Senamirmir Navigation Bar

Printable Page




ምዕላደ-ቃላት



The 6th order vowel is not available either in Ethiopia Jiret, or in most other fonts. The glossary instead represents the 6th order vowel using 'ê'.

Pronunciation


ቃል:HTML (ኤች/ቲ/ኤም/ኤል)
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:Hypertext Markup Language
ቃል:SVG (ኤስ/ቪ/ጂ)
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:Scalable Vector Graphics
ቃል:W3C
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም: የዓለም አቀፍ ዌብ ኮንሰርሽየም (World Wide Web Consortium)
ቃል:XML (ኤክስ/ኤም/ኤል)
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:Extensible Markup Language
ቃል:ልክ
የንግግር ክፍል:ስም
ግሥ:ለካ
ትርጕም:measurement
መጠን።

ቃል:መሥመር
የንግግር ክፍል:ስም
ግሥ:ሠመረ
ትርጕም:line
በሁለት ነጥቦች መካከል በቀጥታና በተናጠል የሚሠረዘው። መስመር ሁልጊዜ ሁለት ጫፎች አሉት። ጫፎቹ መገጣጠም የለባቸውም። በመሆኑም መስመር የሚያካብበው ሥፍራ የለውም።

መነሻ ነጥብ፤ (starting point) ፦ የመሥመሩ መነሻ ሥፍራ።

መድረሻ ነጥብ፤ (end point) ፦ የመሥመሩ መጨረሻ ወይም ማለቂያ ሥፍራ።

ቃል:ምኡዝን (አራት ማእዘን)
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:rectangle
ባራት ቀጥተኛ-ማእዘኖች የተገጣጠሙ አራት ጠርዞች ያሉት ቅርጽ። በጐንና በቁም ሁለት ሁለት ትይዩ ጠርዞች አሉት፤ ወርድና ከፍታ ይባላሉ።

ወርድ፤ (width) ፦ የምኡዝን የጐን ስፋት።

ከፍታ (ቁመት)፤ [ከፈተ] (height) ፦ የምኡዝን በቁም ያለው ርዝመት።

ቀጥተኛ ማእዘን፤ (right angle) ፦ እርስ በርስ በሚተላለፉ ሁለት ቀጥተኛ መስመሮች መካከል ያለው ማእዘን። ልኩ ሁልጊዜ 90 ድግሪ ነው። የ«ማእዘን»ን ፍቺ ተመልከት።

ጥግ፤ [ጠጋ] (corner) ፦ ሁለት መስመሮች የሚጋጠሙበት ሥፍራ።

ቃል:ሦስት ማእዘን (ትሪያንግል)
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:triangle
በሦስት ማእዘኖች የተገጣጠሙ ሦስት ጠርዞች ያሉት ቅርጽ። ሦስቱ ጠርዞች የመሠረት-ጐን፥ የከፍታ-ጐን፥ እና የሰያፍ-ጐን ይባላሉ።

የመሠረት-ጐን፤ (base side) ፦ የትሪያንግሉ የጋድም ጠርዝ። ሉሎች ሁለት ጐኖች የሚቆሙበት።

የከፍታ ጐን፤ (height side) ፦ የትሪያንግሉን ከፍታ የሚፈጥረው ጠርዝ።

የሰያፍ ጐን፤ (hypathenese) ፦ በከፍታ-ጐንና በመሠረት-ጐን መካከል ያለው መስመር።

ማእዘን፤ (angle) ፦ ካንድ ነጥብ በተነሱ ሁለት መስመሮች መኻከል የሚፈጠረው ቅርጽ፥ ክፍትነት። ሀለቱ መስመሮች የተገጣጠሙበት ነጥብ ቨርቴክስ (vertex) ይባላል። መኖሩ የግድ ነው። የቨርቴክሱ ተቃራኒ በሁለቱ መስመሮች መካከል ያለውን ክፍትነትና ዓይነቱን ይወስናል።

ቃል:ርቀት
የንግግር ክፍል:ስም
ግሥ:ራቀ
ትርጕም:distance
በሁለት ነጥቦች መካከል ያለው የቦታ መጠን። በሁለት ነጥቦች መካካል ያለው የቦታ ልዩነት። አባባሉን ለማጥበቅ ያህል፥ የርቀቱ አለካክ በቀጥተኛ መስመር ወይም በጠምዝማዛ ጐዳና ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይችላል።

ቃል:ቅርጽ
የንግግር ክፍል:ስም
ግሥ:ቀረጸ
ትርጕም:shape
አካላዊ መልክ፦ ወርዱ፥ ጐኑ፥ ቁመቱ። ከሥዕል አንጻር ጆሜትሪክ (geometryic) ቅርጾችን ይጠቀልላል። ለምሳሌ መስመር፥ ክብ፥ ምኡዝን፥ ኢልፕስና ሌሎች።

ቃል:ቍጥር
የንግግር ክፍል:ስም
ግሥ:ቈጠረ
ትርጕም:number
ከ0 እስከ 9 ያለው፤ ተደማሪ፥ ተቀናሽ፥ ተባዢ፥ ተከፋይ፥ እና ባጠቃላይ የሚሰላ። ያንድ ነገር ብዛት፥ መጠን፥ ወይም ልክ መግለጫ። ማሳሰቢያ ብዙ የቍጥር ሥርዓቶች አሉ። በዓለም አቀፍ ተቀባይነት ኖረት አሁን የምንጠቀመው የቍጥር ሥርዓት የሂንዱ ሆኖ 10 ሆሄያትን ብቻ ይጠቀማል። የኢትዮጵያ ፊደል የቍጥር ሥርዓት 20 ሆሄያት አሉት።

ቃል:ትዕይንተ-ሥዕል
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:animation
ከሚከተሉትን ተግባራት፥ ቢያንስ አንዱን የሚፈጽም ንባብ፥ ሥዕል፥ ወይም ምስል። ተግባራቱ፦ (1) ልዩ ልዩ እንቅስቃሴ (2) ልዩ ልዩ ሕብረ-ቀለም (3) ትራንስፎርሜሽን፦ ሽክርክርና፥ ዕድገት፥ ጥምዝና የመሳሰለው።

ቃል:ነጥብ
የንግግር ክፍል:ስም
ግሥ:ነጠበ
ትርጕም:point
በማቴማቲክስ ፅንሰ-ሐሳብ ደረጃ፥ ነጥብ አካል የለውም። ነገር ግን በካርትዣን ወይም ተመሳሳይ ሥርዓት፥ ነጥብ ስንል የማንኛውም ግራፍ ትንሹ ክፍል ለማለት ነው። አንድ መስመር በተከታታይ ነጥቦች ይገነባል እንዲሉ።

ቃል:ንባብ
የንግግር ክፍል:ስም
ግሥ:ነበበ
ትርጕም:text
ነፃ አንድ ወይም ካንድ በላይ ቃላትን የያዘ የወረቀት፥ የቃል ወይም ኤለክትሮኒካዊ ጽሑፍ።

ቃል:አሉታዊ
የንግግር ክፍል:ቅጽል
ግሥ:አሉ
ትርጕም:negative
ከ0 (ዜሮ) በታች። የአውንታዊ ተቃራኒ። ላንድ ነገር ተቃራኒ አመለካከት፥ ዝንባሌ፥ ወይም አባባል። የሰሜን ዋልታ አሉታዊ ሲሆን የደቡብ ግን አውንታዊ ነው።

ቃል:አሉታዊ አኀዝ (አሉታዊ ቍጥር)
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:negative number
ከ0 (ዜሮ) በታች የሆነ ቍጥር። ለምሳሌ -1, -2, -3 እና የመሳሰለው።

ቃል:አኀዝ
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:number
ቃሉ የግእዝ ነው። የ«ቍጥር»ን ፍቺ ተመልከት።

ቃል:አውንታዊ
የንግግር ክፍል:ቅጽል
ግሥ:አዎን
ትርጕም:positive
ከ0 (ዜሮ) በላይ። የአሉታዊ ተቃራኒ። ላንድ ነገር ተስማሚ ወይም ተግባቢ አመለካከት፥ ዝንባሌ፥ ወይም አባባል። የደቡብ ዋልታ አውንታዊ ሲሆን የሰሜን ዋልታ ግን አሉታዊ ነው።

ቃል:አውንታዊ አኀዝ (አውንታዊ ቍጥር)
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:positive number
ከ0 (ዜሮ) በላይ የሆነ ቍጥር። ለምሳሌ 1, 2, 3 እና የመሳሰለው።

ቃል:ኢልፕስ
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:ellipse
የx-አክሰስና የy-አክሰስ ርቀቱ በፍጹም አንድ ዓይነት ያልሆነ ክብ። ኢልፕስ የክብ ዘር ነው።

አብይ አክሰስ፤ (major axis) ፦ ከx-አክሰስ ወይም ከy-አክሰስ ርቀት ትልቅ የሆነው።

ንኡስ አክሰስ፤ (minor axis) ፦ ከx-አክሰስ ወይም ከy-አክሰስ ርቀት ትንሽ የሆነው።

የኢልፕስ እምብርት፤ (center of ellipse) ፦ የኢልፕስ መኻከን ነጥብ።

ቃል:ኢንትጀር አኀዝ (ኢንትጀር ቍጥር)
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:integer number
አውንታዊ ወይም አሉታዊ ድፍን ቍጥር፤ ዴስማል የሌለው። ለምሳሌ -3, -2, -1, 1, 2, 3 እና የመሳሰለው።

ቃል:እውን አኀዝ (እውን ቍጥር)
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:real number
ዴስማል ያለው አውንታዊ ወይም አሉታዊ ቍጥር። ለምሳሌ 2.17, 3.14 እና የመሳሰለው።

ቃል:ክብ
የንግግር ክፍል:ስም
ግሥ:ከበበ
ትርጕም:circle
ዙሪያ ያለው ቅርጽ። ከመኻከሉ (ከእምብርቱ) እስከ ጠርዙ በሁሉም አቅጣጫ ያለው ርቀት አንድ ልክ የሆነ።

ዙሪያ፤ [ዞረ] (circumferance) ፦ የክብ ጠርዝ።

ሬድየስ፤ (radius) ፦ ከክብ እምብርት እስከ ጠርዙ በማንኛውም አቅጣጫ ያለው ርቀት።

አካባቢ፤ (area) ፦ በክብ ዙሪያ የተሸፈነው ወይም የታጠረው ሥፍራ።

የክብ እምብርት፤ (center of a circle) ፦ የክብ መኻከል። መስመሮች ከጠርዝ ተነስተው ሁሉም በኩል ርቀት የሚያርፉበት ነጥብ።

ቃል:የሟዚላ ድርጅት
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:Mozilla Organization
ቃል:የቅንብር ሥርዓት (ካርትዣን ቅንብር ሥርዓት)
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:coordinate system
ባለሁለት ድሜንሽን የቅንብር ሥርዓት የሚከተሉት ክፍሎችና ባሕሪያት አሉት።

አክሰስ፤ (axis) ፦ በልክ የተፈረጁ፥ አራት-ቀጥተኛ-ማእዘን ሠርተው፥ እርስ በርስ የተዛመዱ ዐምዳዊና አግድማዊ መስመሮች። አግድማዊ መስመር x-አክሰስ ሲባል ዐምዳዊው መስመር ደግሞ y-አክሰስ። አክሰሶች የሚተላለፉበት በልክ ረገድ እንደ ዚሮ ይቈጠራል።

መነሻ፤ [ተነሳ] (origin) ፦ ሁለቱ አክሰሶች የሚቋርጡበት ነጥብ። ያውንታዊና ያሉታዊ ቈጠራ ከዛ ይጀምራል።

አውንታዊ x፤ (positive x) ፦ በx-አክሰስ ከእምብርቱ ወደ ቀኝ የሚጓዘው ቍጥር

አሉታዊ x፤ (negative x) ፦ በx-አክሰስ ከእምብርቱ ወደ ግራ የሚጓዘው ቍጥር

አውንታዊ y፤ (positive y) ፦ በy-አክሰስ ከእምብርቱ ወደ ላይ የሚጓዘው ቍጥር

አሉታዊ y፤ (negative y) ፦ በy-አክሰስ ከእምብርቱ ወደ ታች የሚጓዘው ቍጥር

ነጥብ፤ (point y) ፦ በሁለት አክሰሶች ሥር ሁለት ሀሳባዊ መስመሮች የሚገጣጠሙበት ወይም የሚያርፉበት። ለተጨማሪ የነጥብን ፍቺ ተመልከት።

x-ፈርጅ፤ (x component) ፦ በx-አክሰስ የተመረጠ ነጥብ ወይም ቁጥር፤ ለምሳሌ ከ(8, 64) ቍጥር 8፥ የx-ፈርጅ ነው።

y-ፈርጅ፤ (y component) ፦ በy-አክሰስ የተመረጠ ነጥብ ወይም ቁጥር፤ ለምሳሌ ከ(8, 64) ቍጥር 64፥ የy-ፈርጅ ነው።

ቃል:ደንብ
የንግግር ክፍል:ስም
ግሥ:ደነበ
ትርጕም:standard; specification; rules
በጋራ ስምምነት ወይም ተቀባይነትን ያገኘ ሕግ፥ አሠራር፥ አጠቃቀም፥ አቀራረብ፥ አሠያየም፥ አገነኛኘት፥ አለካክና የመሳሰለው። እንደ ዩኒኮድ ያለው የፊደል ቦታ አመዳደብ፥ እንደ ቲሲፒ/አይፒ (TCP/IP) ያለው የኢንተርንት መገናኛ መንገድ ድንብ ናቸው።

ቃል:ዴታ
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:data
በመሠረቱ ዴታ ሲባል ያልተበረዘ፥ ያልተዘነቀ፥ ወይም ያልተቀየጠ ብጥር እውን ድርጊት፥ ክንዋኔ፥ ፍጻሜ፥ ሁኔታና የመሳሰሉት ነው። የሰው ስም፥ ትውልድ ቦታ፥ ዕድሜ ወይም ሥራ ዴታ ነው። በSVG ረገድ ግን የ<path> ቃል የሚፈጥረው እያንዳንዱ ቅርጽ የሚያልፍበት ዱካ ወይም ጐዳና ለማለት ነው።

ቃል:ጠርዝ
የንግግር ክፍል:ስም
ግሥ:ጠረዘ
ትርጕም:edge
የወረቀት ዳር ዳሩ፤ የመጽሐፍ መግለጫው፤ የጠሬጴዛ ዙሪያው፤ ወይም የሥዕል ዳር ዳሩ።

ቃል:ፒክስል
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:pixel
ማንኛውም የኮምፕዩተር ሞኒተር ገጽ በጐንና ባምድ (በዐምድ) የተደረደሩ ጥቃቅን ነጥቦች አሉት። በገጹ ላይ የሚታዩት ነገሮች በሙሉ የሚሣሉት እነዚህን ነጥቦች በልዩ ልዩ ቀለም በማብራትና በማጥፋት ነው። እያንዳንዱ ነጥብ «ፒክስል» ተብሎ ይጠራል። የሞኒተሩ ርቅቅና አንድም የሚወሰነው በጐንና ባምድ (በዐምድ) ባሉት የፒክስሎቹ ብዛት ነው። ቲቪም እንዲሁ ነው።

ቃል:ፓዝ
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:path
እያንዳንዱ የሥዕል ቅርጽ ያለፍ ዘንድ የተነደፈ ዱካ (ጐዳና)። ንድፉ ቀጥተኛ መስመር፥ ኢልፕስ፥ ጥምዝ፥ ጥምጥም፥ ወይም ከነዚህ የተወሰኑት ወይም ሁሉም ስብስብ ሊሆን ይችላል።

ቃል:ፖሊላይን
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:polyline
የራሳቸው የሆነ አቅጣጫ ያላቸው የተቀጣጠሉ መስመሮች። «ፖሊ» ማለት «ብዙ» ሲሆን፥ በርግጥ «ላይን» ደግሞ «መስመር» ነው። በመሆኑም ፖሊላይን ሲሉ «ብዙ መስመር» ለማለት ነው። የፖሊላይን የመጀመሪያና የመጨረሻ ጫፎች መገጣጠም አይፈቀድላቸውም። ይህ የፖሊላይን ሕግ ነው።

ቃል:ፖሊገን
የንግግር ክፍል:ስም
ትርጕም:polygon
ጫፎቹ የተገጣጠሙ ፖሊላይን።