XML Overview in Amharic









XML Overview
Introduction
HTML Overview
XML Overview












  


መቅድም

፟ኤማላ፠ (XML) ፥ ኢንተርነትን ይጠቅማሉ ተብለው ከሚጠበቁ አዲስ ቴክኖሎጂዎች መካከል አንዱ ነው። ተግባራዊነቱን ለመጨመር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው። ፟ኤማላ ቁጥር 1.0፠ ከወጣ ከሁለት ዓመት በላይ ሆኖታል። በቅርቡ ማሻሻያ ታክሎለታል። ኤማላ በእንደስትሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት አለው።

...

ኤማላ ብዙ የዓለም ፊደላት ፥ በሌላ አነጋገር ቋንቋዎች ፥ ይቀበላል ፥ ነገር ግን አንዳንድ ፊደላትን ፥ የኢትዮጵያን ጨምሮ ለጊዜው አይደግፍም። ለዚህ ዋናው ምክንያት፥ ኤማላ ሲወጣ ፥ የዩንኮድ ቁጥር 2.0 ቁራኛ እንዲሆን መደረጉ ነው። የኢትዮጵያ ፊደል ፟ዩንኮድ፠ መደበኛ የሆነው ቁጥር 3.0 ላይ ነበረ።

...

አሁን ይህንና የመሳሰሉትን ችግሮች ለማረም ይረዳ ዘንድ፥ በW3C ሰዎች በኩል ለውይይት ውጥን ቀርቧል። ስለዚህ ጉዳይ ወደ መጨረሻ ላይ እንመለስበታለን። ለጊዜው ፥ ስለኤማላ እንነጋገር።

...

የተለያዩ ኮምፕዩተሮች ፥ በኢንተርነት መረብ (ኔትወርክ) ተሳስረው ፥ የዌብ ገጾቻቸውን ላንባቢው የሚያቀርቡት በ፟ሃቴማላ፠ (HyperText Markup Language) ቅርጽ ነው። በመሆኑም ጽሑፍች ፥ መረጃዎች ፥ ሥዕሎች ፥ ድምፆች ፥ እንዲሁም ሌሎች ይዘቶች በቀላሉ ደጃቻችን ይደርሳሉ። ሃቴማላ ፥ የጽሑፎችን አቀማመጥና መልክ ለመወሰን ጥሩ ሆኖ ሳለ፥ የዴታዎችን ማንነት ለመጠቆም ግን ችሎታ የለውም።

...

በሌላ በኩል ፥ ኤማላ (XML) የዴታን ወይም የይዘትን ምንና ማንነት የመደንገግና የመገለጽ ችሎታ አለው። በርግጥ ድንገጋውን የማከናወን ተግባሩ የኛ ነው። ባሁኑ ጊዜ ፥ ውል ላይ የደረሱ ወገኖች ፥ በኤማላ የታቀፉ መረጃዎች መለዋወጥና መቀባበል ይችላሉ። በዚህ ሂደት ውስጥ አብዛኛውን ሥራ የሚፈጽሙት ፕሮግራሞች ናቸው። ፕሮግራሞቹ ፥ በሚሰጣቸው መመሪያ መሰረት የኤማላ ሰነዶች ተቀብለው ፥ ማንነት ተገንዘበው ፥ ተፈላጊ እርምጃ ይወስዳሉ።

...

የዚህ ጽሑፍ ዓላማ፦ 1ኛ) ኤማላን ማስተዋወቅ 2ኛ) ኤማላ 1.0 ለምን የኢትዮጵያን ፊደል እንደማይደግፍ ምክንያቱን ማቅረብ 3ኛ) መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች ፥ አስተያየት መጠቆም ናቸው።



...
smirmir@senamirmir.org
©Senamirmir Project, 2001